ጀ ሰላም ከወራት በፊት አቡነ ማትያስ እንደሚሾሙ ያሳወቀችው እውን ሆኗል፤
አዎን፤ አቡነ ማትያስ 6ኛ ፓትርያርክ ሆነዋል
ደጀ ሰላም
ደጀ ሰላም እያካሄደች ባለችው መደበኛ ያልሆነ “የድረገጽ” ድምጽ አሰጣጥ አቡነ ማቴዎስ ብዙ መራጭ አግኝተዋል፤
ምርጫውን ለሚቃወሙትም፣ ለሚደግፉትም ቀጣዩ ጉዞ እንዴት ይሆናል? እንዴትስ መሆን አለበት?
በውጪ አገራት ካሉ ምእመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያናት የሰከነና የጋራ የሆነ ዘላቂ መፍትሔ ይጠበቃል፤
ውጪ አገር ካለው ሲኖዶስ የበሰለና ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ህልውና የሚበጅ አቅጣጫ ይጠበቃል፤
ድራማው ተጠናቋል፣ ውይይቱ ይቀጥላል።
ምርጫውን ለሚቃወሙትም፣ ለሚደግፉትም ቀጣዩ ጉዞ እንዴት ይሆናል? እንዴትስ መሆን አለበት?
በውጪ አገራት ካሉ ምእመናን፣ ካህናትና አብያተ ክርስቲያናት የሰከነና የጋራ የሆነ ዘላቂ መፍትሔ ይጠበቃል፤
ውጪ አገር ካለው ሲኖዶስ የበሰለና ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ህልውና የሚበጅ አቅጣጫ ይጠበቃል፤
ድራማው ተጠናቋል፣ ውይይቱ ይቀጥላል።

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 21/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 28/2013/PDF)፦ አምስቱን እጩ ፓትርያርኮች ያካተተው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችን ጨምሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ በየደረጃው ድምጽ መስጠታቸው ከተረጋገጠ በኋላ እንደተጠበቀው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም እንዳሸነፉ ይፋ ሆኗል።
ከወራት አስቀድሞ ደጀ ሰላም የውስጥ ምንጮችን ጠቅሳ ባቀረበችው ዘገባ ብፁዕነታቸው የሚቀጥለው ፓትርያርክ እንዲሆኑ በመንግሥት መታጨታቸውን ዘግባ ነበር። በወቅቱ እርሳቸውን ለፓትርያርክነት የሚያሰብ ብዙም ወገን ስላልነበረ የደጀ ሰላም ዘገባ ከተሳሳተ ምንጭ የተገኘ እንደሆነ ብዙዎች ሊያስረዱን ሞክረው ነበር። አሁን ግን “ያልተከደነው ተገለጠ፣ የሚታየው ደግሞ ታየ”።
ለረዥም ጊዜ እንደታየው፣ ብዙዎች ቀጣዩ ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል ይሆናሉ ወይም አቡነ ጎርጎርዮስ የሚል የተሳሳተ ግምት ነበረው። ሁለቱም የጨዋታው አዳማቂዎች እንጂ በጨዋታው ውስጥ ቦታ አልነበራቸውም። ወይም ርዕስ መሆናቸው በራሱ የጨዋታው አንድ አካል ነበር። ብዙ ሰው አሁንም ከጠቅላላው ድራማ አንዱ ክፍል ላይ ብቻ በመከራከር ጊዜውን እያጠፋ ነው። ለአንዳንዶች አቡነ ሳሙኤል ወይም የሚፈልጉት አንድ ሌላ አባት ቢሆን ምርጫውን በደስታ የሚቀበለው ይሆንና አቡነ ማትያስን ሊኮንን ይጀምራል። ጉዳዩ እርሱ አይደለም። ጉዳዩ ቤተ ክርስቲያን ነጻ ናት ነጻ አይደለችም የሚለው ነው። ሌላው ያንን ተከትሎ ይመጣል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደጀ ሰላም ባካሔደችው “ኢ-ቀጥተኛ” የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ከመረጡት መካከል ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በከፍተኛ ድምጽ ተመርጠዋል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሁለተኛነት ሥፍራ አግኝተዋል። ይህ ምን ያሳይ ይሆን? እንመለስበታለን። አስተያየታችሁን፣ ጥያቄያችሁንና ምልከታችሁን ላኩልን። ድራማው ተጠናቋል፣ ውይይቱ ይቀጥላል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን
You may also like - ተመሳሳይ



Search ECADF
Recent Posts
- ተጋዳይ ማትያስ ሹመት ያዳብር
- Melkte Chuchube No 9
- ደጀ ሰላም ከወራት በፊት አቡነ ማትያስ እንደሚሾሙ ያሳወቀችው እውን ሆኗል፤
- የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!
- ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች
- እንደ መጥምቀ ዮኋንስ መንገድ ጠራጊው፤ በሀገረ ብራስል በበልጄይም ከተማ አንዲህ ሲል ተደመጠ…
- የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ
- ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!
- ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል
- የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?
- ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት
- በዋሽንግተንና አካባቢዋ ለምትገኙ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ የስብሰባ ጥሪ፤
- ስርአት አልባው የወያኔ ጋዜጠኛ ከብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል ጋር
- ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)
Widgetized Section
Go to Admin » Appearance » Widgets » and move a widget into FooterLeft Widget Zone
ECADF Hot Links
© 2013, ↑ Ethiopian News in Amharic
© 2013, ↑ Ethiopian News in Amharic
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar