ሃይማኖት፣ ፖለቲካና ህብረተሰብ!
የዐለማችን ሁኔታ በጣም እየተወሳሰበ መጥቷል። በየአገሮች ውስጥ የማህበራዊና የፖለቲካ ጥያቄዎች ሳይፈቱ የሃይማኖት ጥያቄ ራሱን የቻለ አጀንዳ ሆኖ በመምጣት ብዙ አገሮችን እያተራመሰ ነው። በተለይም የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች ውስጥ ያለው የፖለቲካ አወቃቀር ምሁራዊ ብስለት ስለሚጎድለው፣ አፍጠው አግጠው የሚመጡ እንደ ሃይማኖት የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በውውይትና በክርክር ከመፍታት ይልቅ ግብግቡ ወደ አመጽ በማምራት አክራሪዎች በሚባሉትና በመንግስታት መሀከል የሚደረግ ዐይነት ፍጥጫ እየሆነ በመምጣት ላይ ነው። መንግስታት ወደ ዕምነት ያመራውን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል በጭፍኑ በአክራሪነት በመወንጀል በተለኮሰው እሳት ላይ ቤንዚን እየነሰነሱበት ነው። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar