በዚህም የተነሳ በአቶ መለስ “ቀለም ከመቀባት ሌላ የተሻለ ሥራ አልሰራህም” በሚል የተዘለፉትና ከወ/ሮ ሐዜብ ጋር በከፍተኛ ጸብ ውስጥ እንደከረሙ የሚነገርላቸው አቶ አርከበ እቁባይ ከድርጅቱ መሰናበታቸው ተዘግቧል።
መንግስታዊው ሚድያዎች ሳይቀሩ እንደዘገቡት ለዓመታት ፓርቲውን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ያገለገሉት አምባሳደር ስዩም መስፍን ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ፣ አቶ አርከበ ዕቁባይና አቶ ዘርዓይ አስገዶም ባቀረቡት ጥያቄና ፓርቲው እየተገበረ ባለው የመተካካት ሂደት መሰረት በአዲስ አባላት እንዲተኩ የወሰነ ሲሆን አንጋፋ አባላቱ በክብር
ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተሰናብተዋል ቢባልም ስንብታቸው ሕወሓት ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው የውስጥ ችግር ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር ባይኖርም አቶ ስዩም መስፍን በተደጋጋሚ ከሕመም ጋር በተያያዘ ችግር ውስጥ እንዳሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመው ከፓርቲው ራሴን አግልያለሁ ቢሉ እንኳ እንደማይገርም ተናግረዋል።
ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተሰናብተዋል ቢባልም ስንብታቸው ሕወሓት ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው የውስጥ ችግር ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር ባይኖርም አቶ ስዩም መስፍን በተደጋጋሚ ከሕመም ጋር በተያያዘ ችግር ውስጥ እንዳሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመው ከፓርቲው ራሴን አግልያለሁ ቢሉ እንኳ እንደማይገርም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ሕወሓት እነዚህን ነባር አባላት ያሰናብት እንጂ ብ አዴን አሁንም አቶ በረከትን እና አቶ አዲሱን በማ ዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ይዞ እንደሚቀጥል እየተጠበቀ ነው። ከደህዴን በኩል ደግሞ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሁንም የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ የኦህዴድ ምርጫ ውጤት ግን ለነገ ቢራዘምም ለድርጅቱ ማ ዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ከ ጉባኤተኛው እጩ አድርጎ ካቀረባቸው መካከል አቶ አባዱላ ገመዳ ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ ፣ አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፣ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣ አቶ ግርማ ብሩና ደግፌ ቡላ ይገኙባቸዋል ተብሏል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar