ለምሳሌ ከአንዴም ሁለት ጊዜ የኢህአፓን ከፍተኛ አመራር አባሎች ስለፓርቲያቸው ሁኔታ ለህዝብ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ እድል ሰጥቷል ፡፡ ለዶክተር አረጋዊም ሆነ ለሸንጎ መሪዎች እንዲሁ እድሉን ሰጥቷል ፡፡ ጉድለትና ሰንኮፍ ካለበት ደግሞ ኢንስቲትዩሽኑ ወይም ተቋሙ እንዳለ ሆኖ ድክመቱንና ችግሩን አሳይቶ ይበልጥ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እኩል እድሉን ሰጥቶ የኛ አልጀዚራ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በጓሮ በር አሉባልታ መንዛት ራስን ዝቅ ያደርጋል ፡፡ ወደተነሳሁበት ጉዳይ ሳመራ-አንድ ነገር ስለታማኝ ልበል ፡፡ በአንድ አጋጣሚ ዋሽንግተን ዲሲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሳስቀድስ ፣ የታማኝ ባለቤት ሶስት ወንዶች ልጆቹን አቁርባ ስትወጣ አየኋት ፡፡ በፈረንጅ አገር ልጆች የወለደ ሰው ጉዳዩን በቅርበት ይረዳል ፡፡ እንደ አገር ቤት ልጅ የብር ኳስ ሰጥቶ ሂድና ተራኩተህ ና !! የሚባልበት አገር አይደለም ፡፡
እያንዳንዷ ቀን ከልጆች ጋር ስፖርት፥ ኳስ፥ቲኒስ፥ ዳንስ እየተባለ ትንፋሽ የምታስጨርስ ነገር ናት ፡፡ በዚህ ላይ ቅዳሜና እሁድ የትምህርት ቤቶቻቸው ጓደኞች ልጆች ቤት ልደት እየተባለ የሚያልቀው ጊዜ ቀላል አይደለም ፡፡ይህን ሁሉ ጥሎ ከወር በላይ በየአህጉሩ መዞር - ለታማኝ ብቻ የእናት አባቱ እዳ አይደለም ፡፡ ከአሉባልታው በፊት ወሬ የሚያወሩ ሰዎች ! እኔ ይህንን የመሰለ ሥራ መሥራት እችላለሁ ወይ ብለው መጠየቅ አለባቸው ፡፡ በዚህ ቪድዮ ላይ ታማኝ የሚያዝገነዝበውን አቢይ ነገር መስማቱ ራስን እንድንፈትሽ ግድ ይላል ፡፡ በፖለቲካ ፓርቲ አባልነትም ሆነ መሪነት የሚኮፈሱ ሰዎችን ታማኝ ትልቅ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል ውጡና ሥሩ ፡፡ ሠርታችሁ አሠሩ ፡፡ ህዝቡ የት ናችሁ እያለ ነው ብሏል ፡፡
አዎ ብዙ ጊዜ ጭብጨባ አደገኛ ነው ፡፡ ታማኝ ደግሞ የዚህችን ጭብጨባ ምንነት በሚገባ ስለተረዳት- ወደ ትዕቢት እንዳትወስደኝ ፈጣሪዬን እለምናለሁ ብሏል ፡፡ የሠራ ይጨበጨብለታል ፡፡ያልሰራ ደግሞ ራሱ ይንበጫበጫል ፡፡ ኖርዌይ ውስጥ ሌላ አገር የምናየው የሰዎች የኬሚስትሪ አለመግብባትና መናቆር እዚህ ግባ የማይባል ነው ፡፡ እዚህ ኖርዌይ የሚኖር ሰው ደግሞ ጭብጨባ የትም እንደማያደርስ ያውቃል የአገር ቤት ጭቃ ሹምነትን እዚህ አሳዩኝ ማለት ከንቱነት ነው ፡፡ እዚህ በመንገድ ላይ ካርል ዮሃንም ሆነ ኦስሎ ሲቲ የዚህን አገር ቱባ ቱባ ባለስልጣናት እየተጋፋ የሚሄድ ህብረተሰብ ባለበት አገር ፥ የሚያስከብረው ሥራ እንጂ ሹመት እንዳልሆነ ሁሉም ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡ ማጠቃለያው ! ስለዚህ ! ስለዚህ ኢሳት የህዝብ ጆሮና ልሳን ሆኖ እንዲዘልቅ ወገብን ጠበቅ አድርጎ ! ግመሎቹ ይጓዛሉ ውሾቹ ይጮሃሉ ብቻ ነው ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የታማኝን ቃል አድምጡና የአዋራ- አምባው ዳዊትን በኢሳት ላየ የተካሄደ ፕሮፓጋንዳ አፒታይቱ ካላችሁ ሄዳችሁ ጎብኙት
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar