fredag 18. januar 2013
meneger yalebet quTr arat
ጉዳዩ - እሁድ ጃንዋሪ 13 ጠዋት ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በምገኝበት ወቅት
ነው የተከሰተው። የዜጎቻችንን ቁጥር ስለበዛ (አበሻ የሚለውን ቃል መጠቀም ስለሚደብረኝ) ምን ይሆን
ምክንያቱ ብዬ አካባቢውን እየቃኘሁ ፓስፖርቴን አሳይቼ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰሌዳው ላይ የጀርመን አየር
መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንዳለውና መግቢያውም በበር ቁጥር 22 እንደሆነ ይገልፃል።
በተጠቀሰው በር በኩል ሳልፍ በርከት ያሉ ተሳፋሪዎች ተመለከትኩ። አንድ አውሮፕላን ይህን ሁሉ ሰው ይዞ
ይጓዛል? ራሴን በራሴ ጠየቅሁ። መልሱ ብዙም ሰላላስጨነቀኝ ወደ ፊት ቀጠልኩ። እዚህ አካባቢ
የተመለከትኩት የዜጎቻችን ኮተት ማብዛት ፈገግ እያስደረገኝ ወደ ፊት ገሰገስኩ። የፍራንክፈርት አውሮፕላን
ማረፊያ ለንደንን አያክል እንጂ ትልቅ ነው። በተለይ ኮተት ለተሸከመ ሰው አድካሚ የውስጥ ለውስጥ ጉዞ
ይጠብቀዋል።
ለንደን የሚጓዘው አውሮፕላን መግቢያው በር ቁጥር 47 ላይ ስለነበረ ጉዞዬን ቀጠልኩ። በመንገድ ላይ
ተጨማሪ ዜጎቻችን ነበሩ። አንዳንዶቹ የያዙትን ኮተት መጎተት አቅቷቸው እረፍት ለመውሰድ ኮተታቸውን
ከራሳቸው ላይ አራግፈው ቆመዋል። ከተጓዦቹ ማህል አንዷ እንዲውም በጣም ገርማኛለች። ከፍ ያለ ታኮ
ጫማ ተጫምታለች። ቦርሳ አንግታለች፣ ላፕ ቶፕ ተደግሟል፣ አነስ ያለ ቦርሳ ይጎተታል፣ ከውስጥ የተገዛ
ውስኪ በከረጢት ተደርጎ ተይዟል። ልብ ብሎ ለተመለከታት ቤት የምትለቅ ትመስላለች። ይህ ዓይነት ሸክም
በብዙው ተሳፋሪ ላይ የሚታይ ነው።
ሁሉንም መርዳት ሰለማይቻል ጉዞዬን ቀጠልኩ። በመንገድ አንደ ጠና ያሉ ሴት አገኘሁና መርዳት አለብኝ ብዬ
ተጠጋሁ። በትግሪኛ አነጋገሩኝ። እንደማልችል ገልጽኩላቸው። አማራ ነህ አሉኝ። ዘር መቁጠር ሰለማይጥመኝ
ዝም አልኩ። ዘር መቁጠር ብጀምርም ማንነቴን ለመግለጽ እስከ ሰባት ቤት ድረስ መዘዘር አለብኝ። ሸክሙ
ሲቀላቸው አፋቸውን ቀለለው መሰለኝ ጥያቄውን ያዥጎደጉት ጀመር። እኔ ደግሞ ሸክሙ ስለበዛ ለመልሱ
ቦታም አልሰጠሁት።
- አዲስ አበባ ነው እንዴ የምትሄደው ?
- አይደለም። እርስዎ አዲስ አበባ ነው የሚሄዱት?
- አዎ።
- ከሆነ ቦታ ተሳስተዋል። በር ቁጥር 22 ነው’ኮ መግቢያው።
- እሱ ሉፍታንዛ ነው። የእኛ አውሮፕላን 48 ቁጥር ላይ ነው።
- አሁን ግራ ገባኝ ወደ አስመራ የሚሄድ ሌላ አውሮፕላን ያለ መሰለኝ። <<የኛ>> ማለት ምን ማለት እንደሆነ
አልገባኝም።
ወደ መሳፈሪያው በር ላይ ስደርስ ነገሩ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ። አዲሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ
787(Boeing 787 Dreamliner) ፊቱን ወደ መስታወቱ አዙሮ ቆሟል። ከውጭ ሲያዩት ደስ ይላል። ወደ
ሃገሬ ምድር የቀረብኩ መሰለኝ። እቃውን አስረክቤ ሴትየዋን በሉ በሰላም ይግቡ አልኩና ተለያየሁ።
በነገራችን ላይ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀርመን ቅርንጫፍ ሳነሳ አንድ
የማይረሳኝ ነገር አለ። የፍራንክፈርት ባቡር ጣቢያ የሚገኘው መሃል ከተማው
አካባቢ ነው። ከባቡር ጣቢያው ፊት ለፊት የታወቀው ካይዘር
(Kaiserstraße)በመባል የሚታወቀው ሴተኛ አዳሪዎች የሚገኙበት መንገድ
ነው። ከዚህ መንገድ ጎን ደግሞ ሙንሽነር መንገድ የሚባል አለ። በሁለቱ
መንገዶች መሃል አንድ ሕንጻ አለ። ድሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ የነበረው
በዚህ ሕንፃ ላይ ነው። በሕንጻው ላይ በትልቁ የሚል ተጽፎ
ነበር። እሱን ባየን ቁጥር ዜጎች የሃገራችን ስም በፍራንክፈርት እምብርት ላይ
በመለጠፉ እንደሰት ነበር። አየር መንገዱ በደከመ ዘመን እንኳን ይህንን ቢሮ ይዞት ከርሟል። አሁን ግን
በወያኔ ዘመን ይህ ጽሁፍ ከቦታው ወርዷል። የአየር መንገዱም ሥራ ለወያኔ ደጋፊዎች ተበታትኗል። ቢሮውን
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar