lørdag 12. januar 2013
የአበበ ገላው ጉዳይ
ክንፉ አሰፋ
የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በተሰማ ማግስት አንድ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵአዊ ከአውሮፓ ለአበበ ገላው ስልክ
ይደውልለታል። ግለሰቡ ደጋግሞ ሲደውል የአበበ የእጅ ስልክ ጠፍቶ ስለነበር ሶስት ተከታታይ የድምጽ መልእክቶችን
ትቶ ነበር።
“አበበ እባክህን ባስቸኳይ መልሰህ ደውልልኝ። አንተን በተመለከት ከአገርቤት የመጣ መረጃ አለ።እባክህን መልሰህ በዚህ
ቁጥር አስቸኳይ ደውልልኝ።” ይላል መልእክቱ። ደዋዩ ከልብ እንደተጨነቀ ከድምጹ መረዳት ይቻላል።
አበበም በተባለው ስልክ መልሶ ደወለ።
“ሄሎ! አበበ ገላው ነኝ::”
“ሃሎ! አበበ ገላው ነህ?”
“አዎ አበበ ነኝ፣ ማን ልበል?”
“እኔን እንኳን አታውቀኝም፣ ***** እባላለሁ። የምደውልልህ በጣም ጠቃሚ መረጃ ልነግርህ ነው። ግዜ ካለህ አሁን
ማውራት እንችላለን?”
“ችግር የለም ቀጥል።”
“በረከት ስምዖን አዜብ መስፍን፣ እና ብረሃነ ገ/ክርስቶስ አንተን ለማስገደል ማቀዳቸውን ከውስጥ ሰው ተነግሮኛል። እጅግ
በጣም የማምነው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የደህንነት ሰው ነው የነገረኝ። አደራ ባስቸኳይ ንገረው ስላለኝ ነው ደጋግሜ
የደወልኩት። አንተን ለማስገደል ነብሰ-ገዳዮችን ወደ አሜሪካ ልከዋልና ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርግ….”
ደዋዩ ጉዳዩን ለአበበ ብዝርዝር አስረዳው።
አበበ ስልኩን እንደዝጋ የደዋዩን ማንነት ማጣራትና መረጃውን ማረጋገጥ ነበረበት።
በወቅቱ እኔም ቨረጂንያ ነበርኩና ከአበበ ጋር በጉዳዩ ተነጋገርን። ስልክ ከአውሮፓ በመደወል መረጃ የሰጠው ሰው በቅርብ
የማውቀው ወዳጄ ስለነበር፤ ሾልኮ የወጣውን ምስጢር ተአማኒነት በቀላሉ ለማረጋገጥ ቻልን።
መረጃው ትክክለኛ ይሁን እንጂ ነገሩን እንደዋዛ ነበረ ያለፍነው። እነ አቶ በረከት ስምዖን በወቅቱ እጅግ
ተበሳጭተው ስለነበር፤ ስሜታዊ ሆነው በዛቻ መልክ የተናገሩት ነበረ የመሰለን እነጂ እነዲህ አምርረው ነብሰ-ገዳዮችን
አሜሪካ ድረስ ይልካሉ ብሎ ያሰበ አልነበረም። በዚህ - አለም በመረጃ በተጠላለፈችበት ዘመን - የኮ/ል ጋዳፊ
የሎከረቢው አውሮፕላን ፍንዳታ አይነት ወንጀል ለመስራት ማሰብ ከእብደት ውጭ ምን ይባላል?
ያንን የወቅቱ እብደታቸውን የተመለከተ አበበ ገላው ሃገር ውስጥ ቢሆን ስጋውን ዘልዝለው ሊበሉት እንደሚችሉ ጥርጥር
አይኖርም። ለወያኔዎች ጋዜጠኛን መግደል አዲስ ነገር አይደለም። የሉባር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው ተስፋዬ ታደሰን በሩ ላየ
ነበር በሴንጢ ቆራርጥው በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉት። የወላፈን ጋዜጣ አዘጋጅም እስር ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ
እንዲሞት መደረጉ የሚረሳ ጉዳይ አየደለም።
አበበ ገላው በመለስ ላይ ያሰማው የተቃውሞ ድምጽ ህወሃቶችን ለምን በእጅጉ እንዳንገበገባቸው መገመት ግን
ይቻላል።
“ፍሪደም! ፍሪደም! ፍሪደም!....” የሚለው የነጻነት ጩኸት በዚያች በካምፕ ዴቪድ/ሜሪላንድ የስብሰባ አዳራሽ
ብቻ ተወስኖ አልቀረም። አገር-ምድሩ ምስሉንና ድመጹን እየተቀባበለ ከማዳመጥ አልፎ በወቅቱ የሞባይል ፎን ሪነግ-ቶን
ሆኖም ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንባገንኑ ስርዓት ላይ የነበረውን ፍርሃት የሚያስወግድና ለለውጥ እነዲነሳ የሚገፋፋ
መልእክት ስለነበር እነ በረከትን ስጋት ውስጥ ሳይከታቸው አልቀረም።
አነባገነኖች ወትሮውንም ሌላዉን በበላይነት የመናገር እና በሃይል የማሳመን እነጂ የመስማት አቅም የላቸውም። ሌላውን
እነዳሻቸው ይናገራሉ እነጂ ምላሽ አይፈልጉም። አንባገነኖች አፍ እነጂ ጆሮ የላቸውም። ስለዚህ ሰው ሲደፍራቸው
ውድ የኢትዮጳያ የቁርጥ ልጆች በአበበ ገላው ላይ የተሞከርው ሙ ገራ ብያንዳናዳችን ላይ መደርሱ ስላማይ ቀር በማንኛውም፡እንቅስቃሴ በምናደር በት ወቅት አበበን እንደሰለሉት እኛም ከመካክላችን ከተገኙ ለሚመለከተው አካል አሳልፈን የመስጠት ሀላፊነት እንዳልበን መዘንጋት የለበትም .፡፡
ባለፈው ውራትም ኖርዊይ ውስጥ፡የተሰራ አንድ ስራ መረሳት የለበትም ጸረዘረኛየመባለውን ኦርጋናዜሽን ቢሮአቸው ደረስ በመሄድ አቶ ሩነ ባርግ የተባሉትን ግለሰብ ለማስፈራራት የሞከሩ የጉጅሌ ጥርቅሞችን በማንኛወም መንገድ የምሰለል አደል ፈንታ እንዳይ ኖራቸው መቆጣተር ሃላፊነት እንዳለብን ምዘንጋት የለበትም የዚህ አይነት ደድር ጊት ብኛላይ ለመፈጸም ከሞከሩ የምንኖርበት ሓገር የድህንነት ጉዳይ ሙሉ እገዛ እንደሚጋደርግልን እርግጠኛኘኝ ፡፡
ሲሰሩ ካየን መጠቆ፡ያለብኝ፡፡በሖኡን አሳስባለሁ.፡፡
አያና ከበደ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar