lørdag 26. januar 2013

የጥፋት ራእይ፤የክህደት ሌጋሲ፤


                 
ራእይም ይባል ሌጋሲ፤ህልምም ይባል ምኞት አንድ ነገር እውነት ነው። ሰውየው፤ከተጀመረ ጀምሮ በሰላም ኑሮ
እንቅልፍ አግኝቶ ስለማያውቅ ህልም አለመ፤ራእይም ነበረው፤አስቦና መዝኖ ሠራ ለማለት አይቻልም። ከፊቱ ነገ
አልነበረችም። ሊባል የሚቻለው፤ የነበረው የጥፋት፤የማፍረስ፤የመበተን፤የክህደት ቅዠት ብቻ ነው።
የዛፉ ምንነት በሚያፈራው ፍሬ ይመዘናልና፤የተዋቸውን እናስቀጥላለን ከሚባለው ራእይ ባዶ ኳኳታና ጩኸት ማካከል
ጥቂቶችን እንመልከት። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ፤ያልነበረውን እንደነበረ፤ባዶውን እንዳለ፤
የማይሆነውን እንደሚሆን ሲሰበክና ሲቅራራ ሲወሸከት ሕዝብ እንደታዘበ፤ታሪክም እንደመዘገበና የፈጠጠው እውንታ
የሚታይ መሆኑን መካድ አይቻልም። ሚዛኑ፤የሕዝቡ የእለት እለት ኑሮ፤ያለው ነጻነትና መብት፤ስነልቡናው፤የዓለምአቀፍ
ሕብረተሰቡ የሚወተውተው ምን እደሆነ ማየት ነው።
ዓይናችሁን ጨፍሉ ላሞኛችሁ፤እንደሰጎን ራስን አፈር ውስጥ ቀብሮ አልታይም-የብልጣብልጥ ሞኝነት ሲዘበት ሁለት
አስርተ አመታት እንደለፉ፤ በእነዚህ ወርቃማ አመታት መልካም አስተዳደር፤ቅን አመለካከትን ጥረት ታክሎበት አገር
ትመጥቅ ነበር ማለት ምኞት ብቻ ቢሆንል፤ በእድገቷ ከሌሎቹ ቀርቶ ከአአህጉር እህት አገሮች ጋር በተስተካከለች
ነበር፤ምን ያህል ብዙ በተሰራ ነበር ያሰኛል። በእርግጥም ብዙ ሕይወት ተገብሯል፤ሕዝብ ተጎሳቁሏል፤ መብት አልባ
ሖኗል፤ታፍኗል፤ታስሯል፤ተሰዷል፤አገር ተበትናለች፤ንብረት ባክኗል፤ በአገር በሕዝብ ላይ ከመቸውም የበለጠ አደጋ
አንዣቧል።

እውነቱ ሌላ፤የሚወራው ሌላ። ብዙ ጊዜ በማደናቆር፤በመዋሸት፤በማሳሳት፤በተንኮልና ሸፍጥ አልፏል።
ህልምና ቅዠት፤ እውነትና ውሸት፤ማታለል፤መደለልና እውነተኛ ሕዝባዊ አረማማድን ሌለውም ሌላውም ሕዝቡ
በሚገባ ለይቶ ስለሚያውቅ፤ነገ እንደታሪክ እንደሚወራ ማዘንጋት አያሻም። ትላንት ዛሬ ነበረች፤ ዘሬም ነገ ትሆናለች፤
ባጭሩ እንደማንኛውም ስርአት፤ ይኸም ስርአት ይሻግታል፤ይበሰብሳል ያልፋል። እውነታው ግን ለትውልድ ፈጥጦ
ይቀራል።
ከእንግዲህ የሚሞኝ ከተገኘ በራሱ ፈረደ። ወደድንም ጠላንም፤የመዋሸት፤የማታለል፤የክህደት፤የጥፋት ጊዜ፤አብቅቷል።
ሁሉም እርምጃውን ጠብቆ፤ጊዜውን ቆጥሮ ይመጣል። የተሰጋጀም ተዘጋጀ፤ የባከነም በከነ፤ጊዜው ሲደርስ እንደበሰበሰም
ሆነ እንደ እንተዘመመ እንዳልነበረ ሲሆን፤ዞር ብሎ ትላንትን በመልከምም በሌላም መቃኘት አይቀርም። በተለያየ
መልኩ፤ብዙ ዝምታ መስማማት ቢመስልም፤ከምዙ ዝምታ በሗል አበይት ክስተቶች ይኖራል። የሕዝብም ዝምታ ከዚሁ
አይለይም። ዝም አለ ከተባለ ማለት ነው።
ብዙ ሳንርቅ፡ይህ ራእይ እየተባ ሲነገርለትና እንቀጥለው የሚባለው ምኑ ነው? ዲሞክራሲ ቢባል ዲሞከራሲ የለም፤
ነፃነት ቢባል፤ ነጻነት የለም፤መብት ቢባል መብት የለም፤እድገት ቢባል እድገት የለም-የሕዝቡ ኖሮ ምስክር ነውና፤
እንደተባለውም “ምንም የለም”፤ሁሉም የለም። ታድያ እንቀጥል የሚባለው ምኑን ነው? በነበረው በአስ ጉልበት
እንቀጥል ከሆነ፤የሆነው ለመቀጠል አያበቃም፤ቢመኙትም ከሕዝብ ፍላጎት ውጪ ነው። ፊት በሐይል በጡንቻ ነበር፤
የማያስኬድ መንገድም አይደለም። ሃይልም ቢባል፤ የሃይል ምንጭና ሃይል የት እንዳለ ማስተዋል ያስልጋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar