ትላንት ጁምዓ መንግስት በሀረር ከተማ ሙስሊሙ ከጁምዓ ሶላት በኋላ ተቃውሞ ማሰማት ሲጀምሩ በከፈተው ረብሻ ምክንያት የተገደሉትን ንፁሃን ወንድሞቻችንን የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን ሊነዛባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሟች ቁጥሮ እስካሁን እንደታወቀው አራት ሲሆኑ ሁለቱ ከክርስቲያው ወገኖቻችን እንደሆነም ታውቋል፡፡ አንድ በእድሜ የገፉ አዛውንት እና አንድ ወጣት ሙስሊም ወንድሞቻችን ተሰውተዋል፡፡ መንግስት ከረብሻው በኋላ መስጂዱን በፖሊሲ በመክበብ በአካባቢው ማንም እንዳይገኝ መስጂዱን በ20 ሜትር ርቀት ከበው እንዳደሩም ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ ትላንት በሀረር ከተማ መንግስት በፈጠረው ችግር ምክንያት ብዙዎች ለከፋ ችግር ሲዳረጉ አብዛጮች ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ከየመንገዱ እየታፈሱ የተያዙትን የት ቦታ እንደሚወስዷቸው እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፡፡
የግጭቱን መነሻ በቦታው የነበረ ወንድማችን እንደገለፀው “ገና በጧት መስጂዱን በፌደራል የከበቡት ሲሆን የሶላት ሰዓት ሲደርስ ሁኔታውን መቅርፅ ይጀምራሉ፡፡ ሙስሊሙ ሶላት ሰግዶ እንደጨረሰ የተቃውሞ ተክቢራ ሲጀምር ከየት መጣ ያልተባለ ግለሰብ ፌደራሎቹ ጋር በመሄድ በጫማ መማታት ይጀምራል፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ፌደራሎቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ህዝቡ የጥይት ቃታቸውን የሳቡት፡፡” በማለት የግጭቱን መንስኤ ይናገራል፡፡
እስካሁን የመስጂዱን ኮሚቴዎች በሙሉ ያሰሯቸው ሲሆን ቤቶቻቸውንም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ እየበረበሩ ይገኛል፡፡ የትላንናውን ግርግር መንግስት በቪዲዮ በመቀረፅ ለፖለቲካው እንዲመች አድርጎ ለማቅረብ እየተሯሯጠ እንደሆነና በዛሬ ምሽትም በኢቲቪ ሊያቀርበው ዝግጅቱን እንደጨረሰ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ይህን መልእክት ላልደረሳቸው እናዳርስ….
17 minutes ago
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar