ኦህዴድ አባላቱ ዉስጥ የተፈጠረዉን ስር የሰደደ ክፍፍል ለማብረድ ስብሰባ ጠራ
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኦህዴድ አባላት የመጣበትን ከፍተኛ ተቃዉሞ ለማቀዝቀዝ ሙክታር ከድርን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ የይስሙላ ሹመት ቢሾመዉም “ከአሁን በኋላ መታለል በቃ” ብለዉ የተነሱት የኦህዴድ አባላት በተለይ በምስራቅ ኦሮሚያና በሀረሪ ክልል የሚገኙ በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ አመራሮች ፣ መምህራን፤ ርእሰ መምህራንና የወረዳ አስተዳዳሪዎችና አሁንም የተቃዉሞ ድምጻቸዉን እያሰሙ መሆኑን ከወደ ኦሮሚያ ክልል የሚደርሱን ዜናዎች ያስረዳሉ። ይህንኑ ኦህዴድ ዉስጥ የተፈጠረዉን ችግር ለማብረድ በሚል የድርጅቱ አባላት ከህዳር 27 ጀምሮ በሀረሪ ክልል በአሚር አብዱላሂ አዳራሽ መጋቢት 28፣ ቀን 2005 ዓም በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በአቶ ረጋሳ ከፍያለው ሰብሳቢነት ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በምስራቅ ሀረርጌ ደግሞ መካከለኛ አመራር፣ ርእሰ መምህራንና የድርጅት አባላት የተሳተፉበት ተመሳሳይ ስብሰባ በነጋታዉ ተጀምሯል።
በዚህ ከ700 በላይ የሚሆኑ የኦህዴድ አባላት በተሳተፉበት ስብሰባ ዋነኛ የመወያያ ርዕስ ሆነው ከቀረቡት መካከል በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነትና የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በስብሰባዉ ላይ የኦሮሞ ህዝብ በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማንነቱን ያስከበረ መሆኑ፤ ኦነግ የሚያቀነቅነው የመገንጠል ሀሳብ በአንቀጽ 39 የተከበረ መሆኑና በአመራሩ መካከል የታዩ ክፍተቶች የተዘጉ መሆናቸዉ ተደጋግሞ ተስተጋብቷል። ከዚህ በተጨማሪ “የኦነግ አመለካከት ያላቸው ሰርጎ ገቦች” በቂ የስልጣን ቦታ አላገኘንም በማለት የሚያስወሩት ሀሰት መሆኑንና ኦህዴድ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን ማግኘቱን የስብሰባዉ መሪዎች በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኛዉ የስብሰባዉ ተሳታፊ “ ይህ በቂ አይደለም “ ምስራቅ ሀረርጌ በኦሮሚያ ክልል ስር መሆን ሲገባው በሀረሪ ክልል ሆኗል፣ ቋንቋችን ተግባራዊ ይሁን ከተባለ በኋላ እስካሁን ተግባራዊ አልሆንም።” ወያኔንና ለወያኔ የደሩትን የኦህዴድ መሪዎች ያስቆጣ ጥያቄ አቅርበዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar