fredag 14. desember 2012
ለውጥና ማምከኛ የወያኔ ስልት!
ለውጥና ማምከኛ የወያኔ ስልት!
ከዳዊት ዋስይሁን
ለውጥ የተፈጥሮ ህግ ነው። ነገሮች በህዋችን ውስጥ በማያቋርጥ አንቅስቃሴ እና ለውጥ
ላይ እንዳሉ ሳይንሱ አረጋግጦታል። አገራችን እና ሕዝቦችዋ ለውጥን ከተራቡና ከናፈቁ
አመታት ተቆጠሩ። ከዚህ በፊት ህዝቡ ተስፋ ጥሎባቸው ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎባቸው
የነበሩ የለውጥ ወቅቶች በኛ እንዝላልነትና በገዢዎቻችን ብልጣብልጥነት ከእጃችን ላይ
በቀላሉ ሲነጠቁ አስተውለናል። ገዢዎቻችን በጣም ጥንቁቅና የነቁ ስለሆነ እነሱ እጅ
የሚደርስ የመረጃ እና የእንቅስቃሴ ትንሽ የለውም፤ ለደረሳቸው መረጃ አፋጣኝ ምላሽ
ሲሰጡ ለሚጀመሩ ማናቸውም አይነት የለውጥ እንቅስቃሴዎች በጭካኔ በትር
ያኮላሹታል ድጋሚ እንዳያንሰራራ ለሌሎች ትምህርት ይሰጡበታል።
አሁን ግን የሚጠቀምበት ካለ ለለውጡ በከፍተኛ ደረጃ አስተዋጾ የሚያደርግ ፍንጭና
ጅማሬ እየታየ ያለው ከዚህ በፊት በሸሩ፣ በተንኮሉ፡ በከፋፋይነቱ ወደር ከሌለው
ከህውሓት መንደር ውስጥ ሲሆን፤ ይህም ከዚህ በፊት ከህዝብ ዘንድ ተነስቶ በቶሎ
እንደሚታፈነውና ጭላንጭሉን እንደሚያጠፉት ብልጭታ አልሆነም ይልቅስ ከቀን ወደ
ቀን ነገሮች ከቁጥጥር ስር እየወጡባቸው እርስ በራሳቸውም እየተሰላለሉና እየተጠባበቁ
እንዳለ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ጥበቡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው በወያኔዎች ሰፈር የተፈጠረው ድንገተኛ ያልተጠበቀ
አደጋ ወደሚታይ የእርስ በርስ አለመተማመንና መከፋፈል እንደመራቸው በሌላው ወገን
ደግሞ በንሮ ውድነት፤ በፍትህና በመልካም አስተዳደር እጦት፤ በእንግልት እንዲሁም
በሁሉም ማህበራዊ ዘርፍ የተቆላና የተጠበሰ ማህበረሰባች አፋጣኝ ለውጥ ናፋቂ ሲኖር፤
እንግዲህ የተቃዋሚ መሪዎቻችን የመምራት ምህንድስና ሚስጥሩ የሚፈተነው እነኝህን
ሁለት ያፈጠጡ ዋና ግብአቶች አገናኝቶ ለለውጥ ፈላጊው ህዝባችን ጥያቄው ሲመልሱለት
ነው።
በወያኔ መሐል በተፈጠረው ክስተት ካለው እሮሮ ጋር ተዳምሮ በህዝብ ዘንድ የለውጥ
ናፍቆቱንና ረሃቡን ከመቼውም ጊዜ በላይ አጉልቶታል፣ ከዚህም የተነሳ ተስፋ ሰጭ
ጭላንጭሎች ከአራቱም ማእዘን እየታዩ ይገኛሉ። ”አሁን ለውጥ” ”ቀጣይ ሂደት”
”የሚፈጠር ክስተት” ህዝቦችዋ በጉጉት እየጠበቁት ያለው ታላቅ ተስፋዎች ሆነዋል።
ውነትም ያለውን ሂደትና ተጨባጭ ሁኔታውን ስንፈትሸው ወደ አንድ ደረጃ እየደረሰን
እንዳለ ንፋሱ ይናገራል፣ የለውጥ ደመናዎች የመጨረሻ በረከታቸውን ሊለቁ በተጠንቀቅ
እንዳሉ ይመስክራሉ።
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar