መስማት የተሳነው፡ ስብሃት ነጋ
ከማተቤ መለሰ ተሰማ
በአጼ ምኒልክ ዘመን፡ አንድ ኢትዮጵያዊ፡ በድንገት መስማት ይሳነዋል አሉ፡ ሰውየው እድሜ ጠግቦ እስከሚሞት፡ የምኒልክ፣ የእያሱ፣ የዘውዲቱ ንግስና አልፎ፡ ከሀይለ ስላሴ የግዛት
ዘመን አጋማሽ ድረስ ቆይቶ ነበርና፡ ጆሮው መስማት ከማቆሙ በፊት የነበረው ሁሉ እንዳለ፡ የቀጠለ መስሎት፡ በምኒልክ አምላክ እንዳለ ነው የሞተው ይባላል። በአጠቃላይ ስነምግባሩ፡ ሲታይ ከሰው ተወልዶ ከእንስሳት ጋር እንዳደገ፡ በግልጽ የሚመሰክርበት፡ ስብሃት ነጋም፡ እንዳይሰማ ጆሮው የደነቆረው፣ እንዳያነብ አይኑ የታወረው፡ ደደቢት ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም። ምክናያቱም ዛሪ ሕዋሃት የማስመሰያ ካባውን አጥልቆ፡ ኢትዮጵያዊ ለመባል እየጣረ ባለበት ወቅት ስብሃት ከ21 አመት በሗላ የሚናገረው ሁሉ፡ በምኒልክ ሲል እንዳለፈው ሰው ደደቢት በነበረበት ጊዜ ሲሰበክ የነበረውን፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ማዋረድንና አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ማጥላላት፣ ስለአከተመለት ስርአት ሰለደርግ ማውራትን ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ፡ በአሁኑ ወቅት ሰውየውን በጥሞና ለሚከታተለው ሰው፡ ዘመናት ጥለውት ከንፈው እሱ አንድ ቦታላይ ቆሞ ለብቻው እየቆዘመ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግተውም።
ለነገሩማ እርጅናም፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የህሌና ሚዛንን ማዛባቱ ባይቀርም፡ ስብሃትን ግን ከእድሜው በላይ ያደነቆርው፡ ቀን ሲያኝከው የሚውለው ጫት፣ ማታ ተዘፍዝፎበት የሚያድረው አረቄ ነውና፡ እነዚህ ሁለት አድገኛ የሰው ልጅ የአካልም የአእምሮም ጠንቅ የሆኑና አቅልን የሚያስቱ ነገሮች፡ ማየትና መስማቱን ብቻ አይደለም፡ ህይወቱንም አለመንጠቃቸው የሚያስገርም ነው።
ውድ አንባብያን፡ በዚህ ጽሁፊ ስብሃት ነጋን አንተ እያልሁ የምገለጸው፡ የክብርን ዋጋ ለማያውቅና፡ በ90 ሚሊዮን የሚገመተውን ጭዋና አስተዋዩን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ ለሚዘልፍ ሰድ አክብሮት መስጠት፡ እራስን እንደማዋረድ ስለምቆጥረው መሆኑ ይታወቅልኝ። ለምን የሚል ካለ መልሴ፡ ሌላውን ትቸ 19/10/2012 የጀርመን ሶሻሊስት ፓርቲ ባዘጋጀው፡ የአፍሪካ የውይይት መድረክ ሰብሰባ ላይ ተገኝቶ በነበረበት ወቀት ከተናገረው 2ቱን ለአብነት ብጠቅስ በቂ ይመስለኛል። ስብሃት ነጋ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ መጻሂ እድልና የፓለቲካ ምህዳር እንዲያብራራ ለቀረበለት ጥያቄ፡ በተለመደውና ስነምግባር ባልገራው አንደበቱ የሰጠው ከጥያቄው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መልስ፡ 1ኛ/ ስነስራት የሌለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት ለማስተማርና፡ የደርግ እርዝራዦችን፡ ለመቆጣጠር በዙ ጊዜ አሳልፈናል። 2ኛ/ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም የሚል ነበር። ማን ይሆን፣
አውቃለሁ መራር ነው መራብ መጠማት፣
ቁስሉ አይጸናም እንጅ ደግሞ እንደ ውርደት
ያለው? እንዲህ ተዋረደ፡ ደጉ፣ እሩህሩሁ፣ ጭዋው፣ አትንኩኝ ባዩ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ፡ ይገርማል፡ አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ ከወያኔና ጋጠወጥ መሪዎቹ፡ የተመለሰለት ይህ ነው። ለመሆኑ ስብሃት ነጋ ማነውና ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት የሚያስተምረው? እሱስ ስራት ለማስተማረ ቀድሞ ነገር ስራት አለው ወይ? ይህን ያህል በእብሪት የተወጠረበትስ ምክናያት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት የግድ ከሚልበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ከኤርትራዊ እናቱና ከአድዋው አባቱ የተወለደው፡ የዛሪው ስብሃት የትናንቱ ወልደ ስላሴ ነጋ፡ ወደትግል ከመግባቱ በፊት የሚያከብረውና የሚያፈቅረው፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን እንደነበርና፡ አሁንም ሆነ በትግሉ ወቅት፡ ከምር የሰራውና እየስራ ያለው ከኢትዮጵያ የልቅ ለኤርትራ እንደነበርና እንደሆነ በብዙ ማስረጃዎች እያስደገፉ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ የኖሩ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች እነዳሉ አስታውሳለሁ።
ስብሃት ወይንም ወልደ ስላሴ፡ ለኢትዮጵያውያን የነበረውን ጥላቻ፡ በገቢር ማሳየት የጀመረውም፡ ሜዳ በነበረበት ጊዜ፡ ወደትግሉ የሚቀላቀሉ ሴት እህቶቻችንን አስገድዶ እየደፈረ፡ ሲያረግዙ እንዳያጋልጡት በመግደልም እንደነበር ብዙ ቀራቢው የነበሩ ሰዎች ተናግረውታል፡ ቀጥሎ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በሗላም፡ ከመለስ ዜናዊ በስተጀርባ ሆኖ ለ21 አመታት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ለተፈጸመው መለኪያ መስፈርት፡ መግለጫ ቃላት፡ ለማይገኝለት ግፍ፡ ቀላል ሚና አልነበረም፡፡ ሌባ ሲካፈል እንጅ፣ ሲሰርቅ አይጣላም፡ እንደሚባለው ሁሉ፣በቅርብ፡ ከአዜብ መስፍን ጋር፡ በጥቅም መጋጨት እስከጀመሩ ጊዜ ድረስ፡ መለስ ያለስብሃት ይሁንታ፡ የሰራውና የሚሰራው እንዳልነበር የታወቀ ነው።የዛሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ስራት የለውም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም ወ.ዘ.ተ. የሚለው ዘለፋው፡ የመነጨውም፡ከዚያ ከቆየው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ጥላቻው ነው።
ያረጀ የልማድ ፈረስ ጋላቢውና፡ በክፋት፣ በቅናትና በምቀኝነት፡ ለተበከለ፣ በመንፈስም የታወረ፣ በአልኮል መጠጥ ብቻም ሳይሆን፡ በእርኩስ ምኞትም የሰከረ፡ አእምሮ ባለቤት የሆነው፣ እንዲሁም ከክዕደት ጋር ጡት የተጣባው፡ ስብሃት ነጋ፡ የበቀል ጥሙን ለማርካት የነደፈው መረሃግብር ተሳክቶለት፡ ኢትዮጵያ በጥፋት፣ ህዝቧ በፍርሀት እንዲዋጡ፣ ምድሯም ሲቃይ ተዘርቶ መከራ የሚበቅልባት፣ ምሪትና ዋይታ የሚታጨድባት፣ ሞት፣ በሽታ፣ እራብና እርዛት፣ በገፍ የሚመረትባት፣ የሰው ልጅ ስብናው፡ እየበሰበሰ፣ ማንነቱ ሰርዶ እየለበሰ ያለባት፡ ምድራዊ ጋነብ እንድተሆን፡ ካደረጓት ሰዎች ግንባር ቀደሙ ለመሆን በቅቷል።
ያንን ሁሉ በደል ሲፈጽም፡ ዝም በመባሉም ነው፡ እንደዚህ ለከት የለሽ፡ አፉን ለመክፈት የበቃው፡ እኛስ መቸይሆን ትግስታችን የሚያበቃው? መቸ ይሆን ውርደቱ የሚያመን? መቸይሆን በሌሎች ኪሳራ አትራፊ ለመሆን የፓለቲካ ሂሳብ መስራታችንን፡ አቁመን የተነጠቅነውን ማንንታችነን፡ ለማስመለስ የህይወት መሷዕትነት መክፈልን፡ ምርጫችን የምናደርገው? መቸይሆን እንደዚህ እየተዋረዱ፡ ቆሞ ሲሞቱ ከመኖር ይልቅ፡ ሞትን በሞት ሽሮ ማለፍ ሃያው እነት ነው፡ የሚለውን ብሂል ስራላይ የምናውለው? ውድ አንባብያን እስኪ ለአፍታ ቆም በማለት ውስጣችነን እንፈትሽ፡ እኔም፣ አንተም ሆንህ፣ አንች፡ ከስብሃት ነጋ የምናንስበት ምን ነገር አለ?????
ጥቅምት ወር 2012
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar