torsdag 14. mars 2013
Ethiopian community in Belgium (ECB)
ቀን፡ መጋቢት 4, 200( ዓም
በቤልጅየም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት
ጉዳዩ ከኢሳት ጋር ስለተፈጠረው አለመግብባት የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ
ባለፈው ወር መጨረሻ ኢሳት በብራስልስ ባካሄደው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ማህበራችን የወሰደውን አቋም ተከትሎ፣ ኢሳት በሰብአዊ
መብቶችና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከ15 አመታት በላይ በንቃት ሲሳተፍ የኖረውን በቤልጅየም የኢትዮጵያውያን ማህበር የሚያጥላላና
ሐላፊነት የጎደለው ዘገባ ማስተላለፉ ይታወሳል። ማህበሩ በብራስልስ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የቀረበለትን የትብብር ጥያቄ
ያልተቀበለበትን ምክንያት በወቅቱ በጽሁፍ በማሳወቅ አስፈላጊ ከሆነም በግምባር በመቅረብ የማህበሩን ውሳኔ ይዘትና ምክንያት ለማብራራት
ፈቃደኛ መሆኑን አስታውቆ ነበር።
ይሁን እንጂ ኢሳት እስካሁን ለጥያቄው መልስ አልሰጠም፣ ወይንም በማህበሩ ላይ ያስተላለፈው ዘገባ ትክክለኛ አለመሆኑን አላሰወቀም። በሌላ
በኩል ደግሞ በርካታ የማህበሩ አባሎች ትክክለኛውን ሁኔታ በድጋሜ በመግለጽ ኢሳት በማህበሩ ላይ የሰነዘረው አስተያየት የተዛባ መሆኑን
ማሳወቅ አለባችሁ በማለት ጥያቄ በማቅረባቸው፣ ማህበሩ ይህንን ተጫማሪ ማብራሪያ ለማውጣት ተገዷል።
በመሰረቱ የቤልጅየም የኢትዮጵያ ማህበር፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እየተከታተለ ለዓለማቀፉ ማህብረሰብ ማጋለጥ የጀመረው ገና
ኢሳትም ሆነ የኢሳት ባለቤቶች ሳይመሰረቱ እንደሆነ የሚታውቅ ነው። በተለይ ከ1997 ምርጫ በኋላ በህገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተውን መጠነ
ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከትሎ፣ ብራስልስ ዋና የኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ እምብርት በነበረችበት ወቅት ኮሚኒቲያችን የተጫወተውን
ግምባር ቀደም ሚና ሁሉም ዴሞክራሲያዊ ሀይል የሚያውቀው ነው።
ከዚያም ወዲህ ማህበሩ ከአባሎቹ በተነሱ ጥያቄች ተመርኩዞ የውስጥ ደንቡን በማሻሻል የተለያዩ አገልግሎቶችን በመሰጠት ላይ ሲሆን፡ በተለይ
የኢትዮጵያ ቋንቋ መማሪያ ማዕከላትን በማደራጀት በኩል እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ደግሞ በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው። በወቅታዊ አገራዊ
ጉዳዮችና የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ላይም ማህበሩ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ተቀጽላ ሳይሆን እንዲንቀሳቀስ በተሰጠው ውክልና መሰረት
የበኩሉን ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ በኩል የዋልድባን ታሪካዊ ገዳም መከበርና የኢትዮጵያውያን እስላሞች የእምነት ነጻነት መጠበቅ
በሚመለከት፣ በቅርቡ ከሉቅማን የኢትዮጵያውያን እና ቢልጅማውያን እስላምች ማህበርና፣ ከአፋር የሰብአዊ መብት ፎረም ጋር በብራስልስ
የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠቀስ ነው። በአንጻሩ ግን የአርበኞች ግንባርና የግንቦት ሰባት ተወካዮች ነን የሚሉ ግለስቦች ያቀረቡለትን በጋራ
ሰላማዊ ሰልፍ የመጥራት ጥያቄ ማህበሩ አልተቀበለውም። ይህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዓላማና የትግል ስልት ማህበሩ ከተቁቋመበት ዓላማና
መርህ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ባዮቹ ግለሰቦች ያነሱዋቸው መፈክሮች የአብዛኛዎቹ አባሎቻችንን ስሜት
የማያንጸባርቁና አወዛጋቢዎችም በመሆናቸው ምክንያት መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።
በተመሳሳይ ሁኔታ ማህበሩ ባለፈው ወር ከኢሳት የቀረበለትን የትብብር ጥያቄ ያልተቀበለው፣ ኢሳት የአንድ ፓርቲ ልሳን እንጂ ነጻ ሜዲያ
አይደለም፣ በማለት የሚከራከሩ አባሎች በማህበሩ ስላሉ ብቻ ሳይሆን፡ በማህበሩ የውስጥ ደንብ መሰረት የማህበሩ መድረክ የሁለቱ ብድኖች
እሰጥ አገባ መድረክ እንዳይሆን ለመከላከል ጭምር ነው። ከዚህ ውጭ ግን ማንኛውም ቡድን በየበኩሉ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማህበሩ
የሚያከብርና የማይቃወም መሆኑ እየታወቀ፣ በማህበሩ ላይ የተሰነዘረው ክስና በመሪዎቹ ላይ የተከፈተው የማጥላላት ዘመቻ ግን ነውርና
ሀላፊነት የጎደለው ነው። Ethiopian Community in Belgium
Helihavenlaan 55 Bus B2
1030 Brussel
e-mail: Ethiopian.community@gmail.com
URL : http://www.ethiobelgium.com
A/C : 734-0202765-44 , KBC
የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች በራሱ ጥላ ስር እንዲሆኑ፣ አሊያም እንዲዳከሙ ጥረት የሚያደርገውን ያህል፣
ከተቃዋሚ ወገኖችም፣ በፖለቲካ ፕሮግራማቸውና የትግል ስልታቸው ላይ ጥያቄ ያላቸውን ማናቸውንም ስብስቦች በጠላትነት የሚፈርጁ እንዳሉ
ይታወቃል። ማህበራችን ግን ከሁለቱም ወገኖች የሚደርስበትን ጫና እየተቋቋመ ለአባሎቹ የሚሰጠውን አገልግሎትና በአገራዊ ጉዳዮች ላይም
የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደአስፈላጊነቱ የሚቀጥል መሆኑን ለአባሎቹ በድጋሜ ያስታውቃል። ከዚሁ ጋርም በተለይ እንደ ኢሳት ያሉ የነጻ
ሚዲያን፡ የሰብአዊ መብትን እና ዴሞክራሲያዊ እሴቶችን የሚያነሱና የሚጥሉ ወገኖች፣ አንዳንዴ ወደ ውስጣቸውም በማየት የሚሰነዘርባቸውን
ትችት መመርመርና ከሁሉም በላይ ግን የሌሎችንም መብት ማክበር የሚገባቸው መሆኑን ማህበሩ ያስገነዝባል። የተለየ አመለካከት ያላቸውን
ቡድኖች ቀድሞ ከዚህ ወይንም ከዚያ በመፈረጅ ውዥምብር ለመንዛት መሞከር፣ የኢትዮጵያውያንን እንቅስቃሴ የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም
አለመሆኑንም ማህበሩ በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም ወገኖች ያስታውሳል።
በአውሮፓ የተለያዩ አገሮችና ከተሞች የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች፣ በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን ግንዛቤ ይወስዱ ዘንድም፣ ቀደም ሲል
በፌብሯሪ 23 በኢሳት የተላለፈውን የዜና እወጃ እንዲያደምጡ እየጋበዝን፡ ከኢሳት ተወካዮችና ዋና አዘጋጅ ጋር የተጻጻፍናቸውን
ደብዳቤዎችም ኮፒ ያደርግን መሆኑን በህትና እናስታውቃለን።
ከሰላምታ ጋር
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው
ኮፒ
በአውሮፓ የልዩ ልዩ አገሮች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲዎች
በያሉበት
ለኢሳት ዋና አዘጋጅ
አምስተርዳም
በቤልጂዬም የኢትዮጵያ ማህበር በቤልጂዬም ህግ መሰረት በ 14/03/1996 ታትሞ በወጣው ሞኒቶር ጋዜጣ በምዝግባ ቁጥር 4934/
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar