በአደጋ ሰበብ የሕዝብ ትራንስፖርቱን “ሰላም ባስ” በሞኖፖል እንዲይዝ ለማድረግ ሕዝብን ለመከራና ለእንግልት መዳርግ ሥራው የሆነው ኢህአደግ በሚኒባሶች ላይ ማዕቀብ ሊጥል ነው – አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝየኢትዮ-ጂቡቲን የምድር ባቡር መንገድ በማኮላሼት የኢህአዴግ “ትራንስ ኢትዮጵያ እና ጥቁር አባይ” የተባሉት የትራንስፖርት የንግድ ድርጅቶች በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በየዓመቱ እንዲሸቅሉ ሲደረግ – በነዳጅ ዋጋ መጨመርና እና የመጓጓዣ ወጭ መናር የተነሳ መላ የአገሪቱን ህዝብ ለከፋ ኑሮ ውድነት መዳረጉ… ይታወሳል። ኑሮቸውም በዚህ የባቡር መንገድ ተመሥርቶ የነበረው የድሬዳዋ እና የአካባቢው ሕዝብ ለከፋ ድህነት እና ለኑሮ ውድነት እንደተዳረጉ ምንጊዜም የማንረሳው መራር ሃቅ ነው።
የእነኝህ ሚኒባሶች መኖር
1. ብዙ ባለሃብቶች ተፈጥረውበታል፣ በርካታ የሥራ ዕድልም ፈጥረዋል፣ለአገሪቱም ገቢ በማሰገኜት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ፣
2. ተጓዡን ሕዝብ ሳይወጣና ሳይወርድ ቤት ለቤት እየሄዱ ስለሚቀበሉት፣ እንኳን በሌሊት የታክሲ አገልግሎት እንደልብ በማይገኝበት ሁኔታ በቀንም ቢሆን ወደየ አውቶቡስ ጣቢያዎች ለመሄድ መንገደኞች የሚደርስባቸውን እንግልት አስቀርተዋል፣
3. ከጊዜ አጠቃቀም አኳያም ሕዝቡ ጉዞን እንደ ሥራ ሳይቆጥር ሌሊት ሳይቀር ወደ ፈለገው ቦታ በፍጥነት በመድረስ ቀን ሥራውን ሠርቶ ሌሊት ወደ መደበኛ ሥራወ ስለሚመለስ ጊዜውን በአግባቡ ይጠቀምበታል፣
4. ሕጋዊ እየሆነ የመጣው እና በጠራራ ፀሐይ የሚፈጸመው የትራፊክ ፖሊሶች ሙስና አልቻል ባለበት በአሁኑ ወቅት የሌሊት ሙስናውን በር የበለጠ ለመበርገድ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፣
አሁን ደግሞ በመለስ የሙስና ራዕይ (መስረቅም ሥራ ነው አይደል ያለው) የሚንቀሳቀሰው ኪራይ ሰብሳቢው መንግሥታችን፣ የመንጃ ፈቃድ አሰጣጡን ጥራት እና ደረጃ አፈር ድሜ አስገብቶ – “የትራፊክ አደጋ በአስከፊ ሁኔታ የጨመረው በሕገወጦች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ነው” በሚል ሰበብ ሚኒባሶች ከ 150 ኪ.ሜ. በላይ እንዳይጓዙ ቀንም ሆነ ሌሊት የሚጠበቅ ኬላ ሊቋቋም ነው። የተሽከርካሪ አደጋ እንደሆነ በ 5 ኪ.ሜ ውስጥም ሊደርስ ይችላል – የአሽከርካሪዎች ጥራት በዘቀጠበት የአገራችን የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ እና የተሽከርካሪዎች ደህንነት በሙስና በሚታለፍበት የውሸት የቴክኒክ ምመራ ባለበት ሁኔታ።
የሕዝብን መከራና እንግልት ማባባስ ዋና ሥራው የሆነው መንግሥታችን ይህን ለመወሰን ሲያስብ ከልብ በመነጨ የሕዝብ ተቆርቋሪነት ስሜት አይደለም – ዋናው ዓላማ “ሰላም ባስ” የትራንስፖርቱን ዘርፍ በሞኖፖል እንዲይዘው ለማድረግ የታቀደ ነው
1. ብዙ ባለሃብቶች ተፈጥረውበታል፣ በርካታ የሥራ ዕድልም ፈጥረዋል፣ለአገሪቱም ገቢ በማሰገኜት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረጉ ይገኛሉ፣
2. ተጓዡን ሕዝብ ሳይወጣና ሳይወርድ ቤት ለቤት እየሄዱ ስለሚቀበሉት፣ እንኳን በሌሊት የታክሲ አገልግሎት እንደልብ በማይገኝበት ሁኔታ በቀንም ቢሆን ወደየ አውቶቡስ ጣቢያዎች ለመሄድ መንገደኞች የሚደርስባቸውን እንግልት አስቀርተዋል፣
3. ከጊዜ አጠቃቀም አኳያም ሕዝቡ ጉዞን እንደ ሥራ ሳይቆጥር ሌሊት ሳይቀር ወደ ፈለገው ቦታ በፍጥነት በመድረስ ቀን ሥራውን ሠርቶ ሌሊት ወደ መደበኛ ሥራወ ስለሚመለስ ጊዜውን በአግባቡ ይጠቀምበታል፣
4. ሕጋዊ እየሆነ የመጣው እና በጠራራ ፀሐይ የሚፈጸመው የትራፊክ ፖሊሶች ሙስና አልቻል ባለበት በአሁኑ ወቅት የሌሊት ሙስናውን በር የበለጠ ለመበርገድ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፣
በአጠቃላይ የሕዝቡን ሮሮ፣ መከራ እና እንግልት የሚያባብስ፣ ዋና ዓላማው የትራንስፖርት ዘርፉን “ሰላም ባስ” በሞኖፖል እንዲይዝ የታቀደ እንጅ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል የተወሰነ አይደለም – አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
በሰላም ባስ ባለመጓዝ ተቃውሞችንን እንግለጽ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar