torsdag 17. januar 2013
"ሇመሇስ አሇቀስኩ ሇምን ቢለኝ.."
ፓውሌ ኩሌሆ " The Alchemist" በሚሇው መጽሀፉ እንዲህ ጻፈ ፦
ናርሲስ ተወዳዳሪ የላሇው ቆንጆ ወጣት ነበር አለ፤ ከ ውበቱ ጋር ፍቅር ስሇያዘው በእየሇቱ ወዯ አንድ ሀይቅ እየሄዯ
መሌኩን በውሀው ነጸብራቅ ሲያይ ይውሊሌ። አንድ ቀን አጎንብሶ ሲመሇከት አሸንራተተውና ሀይቁ ውስጥ ገብቶ ሞተ።
በማግስቱ የጫካ ንግስት ውሀ ሇመጠጣት ወዯ ሀይቁ ወረዯች፤ ነገር ግን በፊት የምታውቀው የሀይቁ ውሀ ወዯ ጨውነት
ተሇውጦ ሇመጠጣት አስቸጋሪ ሆነ አገኘችው።
የጫካዋ ንግስትም የሀይቋን ንግስት ጠየቀቻት
"ስሇምን እንባዎችሽን ታፈሻሇሽ ? እንባዎችሽ እኮ ውሀውን ጨው አዯረጉብን?"
" ምን ሊድርግ ብሇሽ ነው ናርሲስ እኮ ሞተ "
"አንችማ አሌቅሽሇት ፣ እኔ እሱን ሇማዯን በየጫካው እዞራሇሁ፣ እሱ ዯግሞ ካንጂ ጎን ተዯፍቶ ቁንጅናውን ሲመሇከት
ይውሊሌ። "
" ናርሲሰስ ቆንጆ ነበር እንዴ?" ጠየቀች የሐይቋ ንግስት
" ቆንጆ ነበር ትያሇሽ? ስሇሱ ውበት ካንች የተሻሇ ማን ሉነግረን ይችሊሌ? ካንች አጠገብ አይዯሇም እንዴ ተንበርክኮ
የሚውሇው?"
የጫካዋ ንግስት በሀሳብ ተውጣ ሇትንሽ ጊዜ ጸጥ አሇች።
ቀጠሇች " አየሽ የናርሲሰስን ውበት አንድም ቀን አስተውየው አሊውቅም ነበር፣ ነገር ግን እሱ ከጎኔ መጥቶ አንገቱን
አዘቅዝቆ ሲመሇከተኝ እኔ በእሱ አይኖች ውስጥ የራሴን ውበት መሌሼ ስሇማየው እዯሰት ነበር። ያሇቀስኩትም ሇዚህ ነው።"
መሇስ በተቀበረ በሳሌስቱ ኢህአዴግ ዯስ ብልት" ሇመሇስ ዜናዊ ያነባህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሌዩ ምስጋና ይገባሀሌ" የሚሌ
መግሇጫ አወጣ።
የኢትዮጵያ ህዝብም እንዲህ ሲሌ መሇሰ " አይ ኢህአዴግ ያሇቀስነው እኮ ሇራሳችን ነው። መሇስ የውበታችን ማሳያ ነበር ፤
በእሱ ክፋት የኛን ዯግነት፣ በእሱ ጥጋብ የኛን ረሀብ፣ በእሱ ውሸት የኛን እውነት፣ በእሱ ጉራ የኛን ትሁትነት፣ በእሱ ስድብ
የኛን ጨዋነት እያየን እራሳችንን እያዯነቅን እንጽናና ነበር።"
ኤልን ሳምሶን ( elonsamson@gmail.com)
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar