![]() ዘ-ሐበሻ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልጸዋል::
መንግስትም አቡነ መርቆሪዎስ መንበራቸው ላይ ተመልሰው ማየት እንደማይፈልግ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ግልጽ አቆሙን ያንጸባረቀ በመሆኑ የዕርቁ ጉዳይ ፍጻሜ ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሎል::
በውጭ የሚገኙ አባቶች በዛሬው እለት በሎስ አንጀለስ በጀመሩት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ በትላንትናው እለት ከካናዳ ሎስአንጀለስ ገብተዋል::
ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባቶች አቶ አባይ ጸሀዬ በግልጽ እንዳስታወቁት አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ማለት መንግስቱ ሀይለማሪያም ይመለስ ከማለት ተለይቶ አይታይም ማለታቸው ተሰምቶል::
መንግስት አቡነ መርቆሪዎስ ቢመለሱ ግድ እንደሌለው ነገር ግን ፓትሪያርክ ሆነው ማየት እንደምይፈልግ አቶ አባይ ጸሀዬ አረጋግጠዋል::
ስለሆነም የ 6 ኛውን የፓትርያርክ ምርጫ ሂደት እንዲያፋጥኑ እንዳሳሰቦቸውም መረዳት ተችሎል::
አንዳንድ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ጳጳሳት በተለይም ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመለሱ ከሆነ እኛም አክሱም ላይ የራሳችን ሲኖዶስ እናቆቁማለን በማለት ቤተክርስቲያኒቱን በግልጽ በዘር መስመር ለማስቀመጥ ሀሳብ መሰንዘራቸውን የተገኘው ዜና ያብራራል::
ዕርቁን የሚደግፉና አቡነ መርቆሪዎስን በመንበር ማየት የሚፈልጉ ጳጳሳት ቁጥር እየጨመረ የመጣ ቢሆንም መንግስት አቆሙን በግልጽ ማስቀመጡን ተከትሎ የመንግስት ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ ስብሰባው እንዲጠናቀቅ እየተጠበቀ ነው::
“የሰላምና የአንድነት ፍጻሜው እልባት ካገኘ በኋላ ውጭ ሃገር ከሚገኙት አባቶች ጋር በጋራ የፓትርያርክ
ምርጫውን እናድርግ በሚለው አቋማቸው የጸኑት የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል (ፎቶ)
አባይ ጸሐዬና ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም የተገኙበትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ነው። የቅዱስ
ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ እዝቅኤል ስብሰባውን ረግጠው ለምን እንደወጡና የልዩነት አቋማቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንደሚናገሩ ዝተዋል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የደህንነቶች ክትትል ስር ናቸው!! |

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar