torsdag 10. januar 2013
ወሞረሽ ገኔ የዐማራ ድርጅት ረቡዕ ጥር 1 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅፅ 1 ፣ ቁጥር 8
ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ለመግደል የተደረገው ሙከራ፣
የወያኔ ዐማራን አድኖ የማጥፋት ዘመቻ አካል ነው!
ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰጠ መግለጫ
በትላንትናው ዕለት ማክሰኞ ታኅሣሥ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ወያኔ በነባር ነፍሰ ገዳዮቹ ፣ በእነርሱ አጠራር
“ፈዳያኖቹ” ፣ አማካኝነት ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነውን አበበ ገላውን ለመግደል አቅዶት የነበረውን ዕቅድ
በአሜሪካ የፌደራል የመረጃ ቢሮ (FBI) ክትትል የመክሸፉን አስደንጋጭ ዜና ሠማን። ‘ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
(ሞወዐድ)’ ይህንን የነፍሰ-ገዳይ ወያኔዎችን ድርጊት የሚመለከተው በታላቅ የመናቅ ፣ የመደፈር ፣ የመሣደድና የመቆጨት
ስሜት ነው። ድርጊቱ ወያኔ በዐማራው ሕዝብ ላይ ሠንቆት የተነሣው የዘር ጥላቻ የቱን ያህል የከፋና ሥር የሠደደ እንዲሁም
ወያኔ የዐማራውን ዘር ከምድረ-ገጽ ሣያጠፋ እንቅልፍ ሊኖረው እንደማይችል ማረጋገጫ ነው። የትግሬ-ወያኔ ግድያውን
ለመፈፀም አቅዶ መንቀሣቀሱ በራሱ እኛን ዐማሮችን የቱን ያህል የናቀንና የደፈረን እንደሆነ አመላካች ነው። በሌላ በኩል
የግድያውን ዕቅድ ተከታትለው የደረሱበት ወገኖች አኩሪ ተግባር ያሉንን የወዳጅ ምሥክሮች ዕርዳታ ያረጋግጥልናል።
ትግሬ-ወያኔዎች በዘር ተደራጅተው እኛን የደፈሩን ፣ ያዋረዱንና ያሣደዱን በቁጥር ‘ብዙኃኖቹ’ ስለሆኑ አይደለም።
አገራችንን ጥለን በብዙ ርቀት በስደት በምንኖርበት አገር ሣይቀር እየተከታተሉ አንገታችን እንድንደፋና አፋችን እንድንዘጋ
ያደረጉን መለኮታዊ ኃይል የተጎናፀፉ ስለሆኑ አይደለም። ይኸን የመሰለ የከፋ ርምጃ ሲወስዱ እያየን ብዕራችንን እንዳናነሣና
ተቃውሟችንን እንዳንገልፅ ስላደረጉን አይደለም። ወያኔዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸው የበለጠ እንዲንቁን ፣ እንዲያዋርዱንና
እንዲያጠፉን ሠፊ በር የከፈትንላቸው እኛው ራሣችን ዐማሮች ነን። በዐማራነታችን ተደራጅተን ፣ የራሣችንንና የወገኖቻችንን
ሕልውና ከማስጠበቅ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ስም ተደብቀን ፣ በወያኔ የዘር ፖለቲካ ከተጠመቁ ዘረኛ ትግሬዎችና መሰል
የጎሣ ፖለቲካ አራማጅ ድርጅቶች አባላት ጋር የምናደርገው መሞዳሞድ ራሣችንን አስንቀን በሌሎችም እንድንናቅ
አድርጎናል። ይህም እኛ ለዘራችንና ለወገናችን ሞትና ችግር የማይሰማን ፣ የማንማረርና የማንረባ ሆድ-አደር እንስሶች
እንደሆንን አድርገው እንዲመለከቱን ገፋፍቷቸዋል። “ቃጣኝ ፣ ልትሰድበኝ አስበሃል” ብሎ ፤ በክፉ ያዬውን ሰው ደረት
ወይም ራስ አነጣጥሮ ተኩሶ ከሚጥል ፤ የአገርና የወገን ጠንካራ ዘብ ከነበረ ነገድ ተወልደን ሣለ ፤ ዛሬ እኛን ሲገድሉን ፣
አስረው ሲቀጠቅጡንና የነገዳችን ስም እየተጠራ ስማችንን ጥላሸት ሲቀቡት ፤ ዐይተን እንዳላየንና ሰምተን እንዳልሰማን
መሆናችን ለወያኔዎች የልብ ልብ ሰጥቷቸዋል። ስለሆነም የሕግ የበላይነት በሠፈነበት አገር ድረስ መጥተው የእነርሱን
የበላይነትና አይፈሬነት ሊያሣዩን ግድያ እስከማቀነባበር ደርሰዋል።
ወያኔዎች የሚቃወሟቸውን ሰዎች ነፍሰ-ገዳዮቻቸውን ወደውጭ አገሮች ልከው ንፁሕ ሕይወት ማጥፋት ለእነርሱ
አዲስ ነገር አይደለም። ወያኔ በነፍሰ ገዳዮቹ አማካኝነት ድንበር አቋርጦ ኬንያ ይኖሩ የነበሩትን በርካታ ተቃዋሚዎቹን
MORESH WEGENIE AMARA ORGANIZATION
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910
Tel: (202) 230 - 9423 Fax:
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar