tirsdag 18. februar 2014
የአባይ ግድብና የአገዛዙ ተቃርኖዎቹ (ቴዎድሮስ ጌታቸው – ከኦስሎ)
የአባይ ግድብና የአገዛዙ ተቃርኖዎቹ (ቴዎድሮስ ጌታቸው – ከኦስሎ)
በአለም የወንዞች ታሪክ እንደ አባይ የተዘፈነለት፤ የተዘመረለት ወንዝ ያለ መቸም አይመስለኝም በአለም በእረጅምነቱ የሚስተካከለው የሌለው አባይ በትውልድ ሃገሩ ከዘፈን ግጥምና ከእንጉርጉሮ አድማቂነት ያለፈ ጥቅም ሳይሰጥ ለዘመናት ያለማቋረጥ መፍሰሱ እርግጥ ነው። ከወቀሳ እስከ ሙገሳ ከቁጭት እስከ ብስጭት ብዙ ብዙ ተብሎለታል ለአባይ ያልዘፈነ ዘፋኝ ያልገጠመ ገጣሚ ያልተቀኘ ባለቅኔ ማግኝት ይከብዳል እናም አባይ ለቁጥር የሚታክቱ የስነጥበብ ጉዳዮችን አስተናግዷል። Read full in PDF: የአባይ ግድብና ተቃርኖዎቹ
ግብጽ ከሩሲያ ጋር የ2 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ተደራደረች

በመጪው ምርጫ የግብጽ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ የሚባሉት የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ፊልድ ማርሻል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሩሲያ ጋር የ2ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ድርድር ላይ መሆናቸው በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡
ረቡዕ ሞስኮ የገቡት አል-ሲሲ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር የመሣሪ ውሉን በተመለከተ የሁለት ለሁለት ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ ከግብጽና ከሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የድርድር ውሉ ዋና አካላት ናቸው፡፡
“ጉብኝታችን በግብጽና ሩሲያ መካከል የወታደራዊና የቴክኖሎጂ ልማት ስምምነት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ መክፈት ይሆናል” ያሉት አል-ሲሲ ትብብሩን ለማፋጠን ተስፋ እንዳለቸው ጠቁመዋል፡፡
ይጸድቃል የተባለው ይህ ስምምነት ከሩሲያ በኩል ድጋፍ እንዳለው ፕሬዚዳንት ፑቲን አል-ሲሲን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡ “የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን የምርጫ ውድድር ለማድረግ መወሰንዎን አውቃለሁ፤ በራሴና በሩሲያ ሕዝብ ስም መልካሙን ሁሉ እመኝልዎታለሁ” ብለዋል ፑቲን፡፡
በዚህ ስምምነት መሠረት ግብጽ ዘመን ያለፈባቸውን ሩሲያ ሰራሽ የጦር መሣሪያዎቿን በአዳዲስና ዘመናዊ መበተካት ወታደራዊ ብቃቷን በከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ እንዳሰበች ማረጋገጫ ነው የሚሉ ወታደራዊ ተንታኞች ይህ የግብጽ አካሄድ በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ አፍሪካ የሚያመጣው ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ስምምነቱ ይፋ ከሆነ በኋላ በሚወጡ መረጃዎች ዝርዝሩ የሚታይ እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች እንዲህ ዓይነቱ ሚሊታሪዝም (ወታደራዊ ተስፋፊነት) ግብጽ በተለይ በአቅራቢያዋ ባሉ አገራት ላይ ልታራምደው የምታስበውን ፖሊሲ የሚጠቁም እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ብዙዎቹንም ከፍተኛ የዓቅም ፈተና ውስጥ ይከታቸዋል ተብሎ ይገመታል፡፡
(የጎልጉል ዜና የተጠናቀረው ከAFP)
የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአውሮፕላን ጠለፋ የአለም መነጋገሪያ በመሆን ቀጥሎአል
February 18, 2014 Comments Off
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 702 የሆነውን አውሮፕላን በመጥለፍ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ እስካሁን ድረስ የጠለፋውን መንስኤና ምክንያት በግልጽ የመናገር እድል ባለማግኘቱ የአለም የመገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። አንዳንዶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አስከፊ ጭቆናና ፓይለቱ አውሮፕላኑን እንዲጠልፍ እንዳነሳሳው ሲገልጹ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ጥገኝት ለመጠየቅ ተብሎ ከተደረገ ስህተት ... Read More »
ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል
